ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት በምሥራቅ አማራ ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት ድጋፍ አደረገ።

25

ደሴ፡ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው በምሥራቅ አማራ ለሚገኙ ለተለያዩ የጤና ተቋማት እና የችግሩ ሰለባ ለኾነው አርሶ አደር የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች እየሠራ መኾኑን ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ገልጿል።

የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የቤኤችኤ ፕሮጀክት የፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር አበባዉ ሲሳይ ለ14 ጤና ተቋማት የሚኾን የህክምና ግብዓቶች የሲቢሲ እና የኬሚስትሪ ማሽኖችን ጨምሮ 17 አይነት ግብዓቶችን ከ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ለግብርናውም ዘርፍ የአርሶ አደሩን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱ ግብዓቶች እንደ ምርጥ የአትክልት እና ፍራፍሬ ዘር የውኃ መሳቢያ ሞተሮች እና የጉድጓድ ውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ጨምሮ ለአርሶአደሩ እንሰሳትን እና ከ11ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸውን ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አበበ ተምትሜ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ ለማቋቋም እንደ ሀገር በርካታ ሥራወች ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ተቋማትን ለማቋቋም ከሚያግዙ አጋር አካላት መካከል ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ይጠቀሳል ብለዋል።

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለጤና ተቋማቱ ያደረገው ድጋፍ ከፍተኛ መኾኑን ገልጸው ለድጋፉም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ማህሌት ተፈራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለባለሃብቶች ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ እና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የተጀመረው የልማት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አህመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ገለጹ።
Next article” አዲስ ውበት፣ አዲስ ሀሴት”