የአዘዞ -አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ቀሪ የአስፓልት ንጣፍ ሥራን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

17

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ እንደገለጹት የአዘዞ አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ግንባታውን አስጀምሯል።

ከተማ አሥተዳደሩ ከሦስተኛ ወገን ጋር በተያያዘ ችግሮች የነበሩበት ቢኾንም ከከተማ አስተባባሪ ኮሜቴው ጋር በመወያየት ሂደቱን የሚከታተል ጠንካራ አመራር ተመድቦ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ከነበረበት መፋዘዝ ወጥቶ በግንባታ መነቃቃት፣ የግብአት ማጓጓዝ እንዲሁም የአስፓልት ንጣፍ የጀመረበት ሁኔታዎች መኖሩን አስረድተዋል።

የመንገዱ ቀሪ አራት ኪሎ ሜትር የአስፓልት ንጣፍ ሥራ ጥራቱን ጠብቆ እሰከ ሐምሌ/2016 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ለመሥራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል አካል የሚከታተለው የአዘዞ አርበኞች አደባባይ መኾኑን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መኾኑ ታውቆ የሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ርብርብ እንዲያደረጉ መልዕክት ያስተላለፉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እንደ ከተማ የሚጠበቀውን ከሦስተኛ ወገን የማጽዳት ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱን የመከታተል እና የአካባቢውን ጸጥታ የመጠበቅ ሥራን ኀብረተሰቡ በደስታ ተቀብሎ እየሠራ እንደሚገኝ ነው ያብራሩት።

እነደ ጎንደር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ በግንባታው ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች የነገ ታሪክ በመኾኑ አምሽቶ በመሥራት እና ቀደመው በመግባት ርብርብ እንዲያደረጉ እና የከተማው ሕዝብም የአካባቢውን ጸጥታ በመጠበቅ መንገዱ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየከንቲባ ችሎት አገልግሎት የበርካታ ዓመታት የሕዝብ ጥያቄዎችን እየፈታ መኾኑን ተገልጋዮች ገለጹ።
Next articleየልማት እና የገቢ አሠባሠብ ሥራዎችን አፈጻጸም ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።