“ሚዳ እምርታ የተሰኘ ኘሮጀክት ለብዙዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ፕሮጀክት ነው” አቶ አሰፋ መንግሥቱ

16

አዲስ አበባ: ግንቦት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሚዳ እምርታ የተሰኘ ኘሮጀክት ለብዙዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ፕሮጀክት መኾኑን የፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አሰፋ መንግሥቱ ተናገሩ፡፡ ሚዳ እምርታ የተሰኘ ኘሮጀክት የፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ አካሂዷል። ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል በተለይም በደቡብ ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞን ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም በምርቱ ላይ እሴት ጨምረው ለገበያ እንዲያቀርቡ እያደረገ አምራቾች፣ ነጋዴዎች እና አቀናባሪዎች የተሻለ ገቢ እያገኙ ድህነትን ለመቀነስ እየሠራ ያለ ተቆም ነው።

የፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አሰፋ መንግሥቱ ለማ ሚዳ እምርታ ፕሮጀክት በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በሦስት ወረዳዎች በፎገራ፣ ሊቦከምከም እና ደራ ወረዳዎች የሩዝ እና የአትክልት ምርቶችን፤ በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ በከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ እየሠራ እንደኾነ ተናግረዋል። ሚዳ እምርታ ፕሮጀክት ለአቀናባሪዎች እና ለነጋዴዎች የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ምርቱ በብዛት የሚቀርብበትን መንገድም እያመቻቸ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ ለብዙዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ፕሮጀክት መኾኑን አቶ አሰፋ መንግሥቱ ገልጸዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የአትክልት እና ፍራፍሬ ግብይት አማካሪ ዓለማየሁ ታደሰ ፕሮጀክቱ በሚሠራባቸው የግብርና ዘርፎች የተለያዩ የምርጥ ዘር ዓይነቶችን በማባዛት ለአርሶ አደሮች እና ለተጠቃሚዎች በማዳረስ ተጠቃሚ እያደረገ ያለ ፕሮጀክት መኾኑን ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጸጥታ ችግሩ የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እንዲስፋፋ እያደረገ መኾኑ ተመላከተ፡፡
Next article“በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እየተሻሻለ መምጣቱን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።