“በፓርኩ ያየነው የሥራ እንቅስቃሴ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ትልቅ ተቋም እየተገነባ መኾኑን ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

19

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብሔራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤቱ በአንደኛ መደበኛ ስብሰባው ያሰቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ትግበራ ገምግሟል፡፡ በቀጣይ ደግሞ በዲጂታል ምህዳሩ የወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ የአሠራር መመሪያዎች እና ሌሎች ዶክመንቶች አሁን ካለው የመንግሥት ሁሉን አቀፍ ሪፎርም፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚናበቡ እና የሚጣጣሙ መሆናቸው ተጠንቶ እንዲቀርብ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ልማትንም ጎብኝቷል። ያሉበትን ውስን ተግዳሮቶች በመፍታት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እና ከመንግሥት ጋር ያለውን ትብብርና መደጋገፍ የሚያጠናክር ቁመና እንዲላበስ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል ብለዋል።
አቶ ተመስገን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ በዳታ ሴንተር ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ድርጅቶችን እና የኢንኩቤሽን ማዕከልን ጎብኝተናል ብለዋል።

የተመለከትናቸው ድርጅቶች በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት አስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልተው ዝግጅት ከማጠናቀቃቸውም በላይ ለደንበኞቻቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተመልክተናል ነው ያሉት። በአጠቃላይ በፓርኩ ያየነው የሥራ እንቅስቃሴ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ትልቅ ተቋም እየተገነባ መኾኑን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየእንስሳት ሃብት ዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
Next article“ከየትኛውም የሀገራችን አቅጣጫ የሚመጡ ጥቃቶችን ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ተገንብቷል” ጄኔራል አበባው ታደሰ