እስካሁን ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አማራ ክልል መግባቱን የግብርና ቢሮ ገልጿል፡፡

13

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን 5 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን 169 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል። በምርት ዘመኑ የታቀደውን ግብ ለማሳካት ከሚሠሩ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል አንዱ ማዳበሪያ በወቅቱ እና በሚፈለገው ልክ ለአርሶ አደሮች ማቅረብ ነው። ይህ ሲሆን ምርታማነት ይጨምራል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም ፈተና አይኾንም።

ለአማራ ክልል ለምርት ዘመኑ 8 ሚሊዮን 057 ሺህ 900 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ታቅዶ ግዥ ተፈጽሟል። ከተገዛው ውስጥ ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደብ የደረሰ ሲኾን ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ደግሞ ወደ ክልሉ ገብቷል። 3 ሚሊዮን 936 ሺህ 397 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከዩኒየኖች ወደ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተጓጉዟል። እስካሁን ባለው አፈጻጸም 3 ሚሊዮን 547 ሺህ 340 ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ማሰራጨት ተችሏል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው ክልሉ ከገባለት የአፈር ማዳበሪያ 78 በመቶ ለአርሶ አደሮች አሰራጭቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመነኾሪያ አገልግሎትን ለማዘመን እየተሠራ ነው” በሰሜን ወሎ ዞን
Next articleየእንስሳት ሃብት ዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡