
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በ2016 ዓ.ም 30 ሺህ 140 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መካከል አንዱ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ነው፡፡ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት በተያዘው በጀት ዓመት ከ250 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ከ151 ሺህ ሄክታሩን በዘር መሸፈን ተችሏል፡፡
የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሚከናወኑባቸው አካባቢዎች አንዱ የሰሜን ሸዋ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ግብርና መምሪያ የአትክልት፣ ፍራፍሬ እና መስኖ ውኃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አስካል ይፍሩ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ 39 ሺህ 646 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 30 ሺህ 140 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻላቸውን ገልጸዋል። እንደ ግብርና ቢሮ መረጃ በዞኑ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!