“ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተው አዲሱን የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር ለማጠናቀቅ ዛሬ አስጀምረናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

18

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊዎች ለዜጎች ህይወት እና ከባቢ መለወጥ ያለመታከት ልግስናቸውን እንዲዘረጉ መልእክትም አስተላልፈዋል። ሥራውን አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣዩን መልእክት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። ዛሬ በአዋሬ አካባቢ ከስድስት ዓመታት በፊት በጀመርነው የዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ ምናልባትም የመጨረሻው ስፍራውን ለግንባታ ዝግጁ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል።

የመኖሪያ ሁኔታዎቹ ችግር የበዛባቸው ነበሩ። እጅግ ያረጁ፣ የተጠባበቁ፣ መፀዳጃ የሌላቸው መኖሪያዎች ነበሩ። ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተው አዲሱን የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር ለማጠናቀቅ ዛሬ አስጀምረናል። ይህ ሥራ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ህይወት ብቻ ሳይሆን የሪል ስቴት አልሚዎችንም የጠቀመ ነው። በዚህ ፕሮጀክት የቀጣይነት መንፈስ አይተንበታል።

አፅንተንበታልም። አዋሬ ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረት የመኖሪያ አካባቢዎችን ሊለውጥ የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ እና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው። የዚህ አመቱ የዝቅተኛ ቤቶች ግንባታ ወጪ በከፊል በቪዛ ፋውንዴሽን (VISA Foundation) ተሸፍኗል። ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊዎች ለዜጎች ህይወት እና ከባቢ መለወጥ ያለመታከት ልግስናቸውን እንዲዘረጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገር በቀል ዕውቀቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ምሁራን በሳይንሳዊ መንገድ ጥናት ሊያደርጉባቸው ይገባል” የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር
Next articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አፅቀሥላሴ ከሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ።