162 ሄክታር መሬት በሁለተኛ ዙር መስኖ እየለማ መኾኑን የቆቦ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታዎቀ፡፡

17

ወልድያ: ግንቦት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)አርሶ አደሩ የመስኖ አጠቃቀም ልምድን በማዳበሩ በዓመት ሦስት ጊዜ ማምረት እንደተቻለ የቆቦ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ጉግሳ ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ የ2015/16 የመኽር ምርት ከሠበሠበ በኋላ በአንደኛ ዙር መስኖ አምርቷል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ደግሞ የሁለተኛ ዙር መስኖ እና የዓመቱን ሦስተኛ ዙር ምርት በማምረት ሥራ ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።

162 ሄክታር መሬት በሁለተኛ ዙር መስኖ እየለማ እንደሚገኝም ነው ያብራሩት። ከዚህ ውስጥ 73 ሄክታር በአትክልት፣ ዘጠኝ ሄክታር በቅመማ ቅመም ቀሪው በማሾ እና በአዝዕርት እንደተሸፈነ ኀላፊው ነግረውናል። 18 ሺህ 599 ኩንታል ምርት ለመሠብሠብ መታቀዱንም ገልጸዋል።

የታቀደውን ምርት ለመሠብሠብ ይቻል ዘንድ ከማዳበሪያ አቅረቦት ባሻገር ከወረዳ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች አርሶ አደሩን እየደገፉ መኾኑን ነው ያስረዱት። ማሳቸውን ሲንከባከቡ አሚኮ ያገኛቸው አርሶ አደሮች በተያዘው ዓመት ለሦስተኛ ጊዜ ምርት ለማስገባት እየሠሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ በአንደኛ ዙር መስኖ የተሻለ ምርት ማግኘታቸውን ገልጸው በሁለተኛው ዙር መስኖ ውጤታማ ለመኾን በትጋት እየሠሩ መኾኑን ነው የገለጹት።

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርሶች ቀን በጢያ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ሊከበር ነው።
Next articleወሎ ዩኒቨርሲቲ ሂዩማን ብሪጅ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።