
በባሕር ዳር ከተማ ባለሀብቶች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የእጅ መታጠቢያ ሳሙናና ውኃ እያቀረቡ ነው፡፡
የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በነጻ የሚያድል ባለሀብትም ተመልክተናል፡፡ ይህን በጎ ተግባር ሁሉም በየአካባቢው ቢተገብረው የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ትልቅ ድርሻ ማበርከት ይቻላል፡፡
እርስዎስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ምን ያህል እየተጠነቀቁ፣ ምን በጎ ተግባርስ እያከናወኑ ነው?
ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል፡-
• እጅዎን በንጹሕ ውኃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፤
• እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ ዓይንና አፍንጫዎን አይንኩ፤
• ከሰዎች ጋር አይጨባበጡ፤
• ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል ይራቁ፤
• ሰዎች ወደሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የሕመም ስሜት ካለብዎት አይሂዱ፤
• በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፤
• የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፤
• በሥራ ቦታ፣ “በትራንስፖርት” እና በመኖሪያ ወይም በመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፤
• የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ በነጻ የስልክ መሥመር 8335 መደወል ይችላሉ፡፡
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት