ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎበኙ።

22

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህና ሚኒስትሮች ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎብኝተዋል። የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።

ዓመታዊው ኤክስፖው “ሳይንስ በር ይከፍታል፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ኃሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ ይገኛል። የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርት አፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለዕይታ አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት መንግሥት በነዳጅ እና ማዳበሪያ ላይ ድጎማዎችን እያደረገ እንደሚገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የመገናኛ ብዙኀን የላቀ ሚና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ