
አዲስ አበባ: ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቻይና-አፍሪካ የከፍተኛ ባለሙያዎች የትብብር ኮንፈረንስ (FOCAC) “ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካዊ ወካይ ድምጽ የነበራት ሚና ከትናንት እስከ ዛሬ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ኮንስለር ሚስተር ያንግ ይሃንግ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተች እንደኾነ አንስተዋል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የእስያ እና የፓሲፊክ ጉዳዮች ምርምር ጄኔራል ዳይሬክተር አንተነህ ጌታቸው (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በትብብር ኮንፈረንሱ ውስጥ እንደ አፍሪካዊ በነበራት ወካይ ድምጽ ግንኙነቱ እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በትብብር ኮንፈረንሱ ውስጥ ላለፉት 24 ዓመታት የራሷንም የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን የጋራ ጥቅም ባከበረ መልኩ እየሠራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በኮንፍረንሱ የተለያዩ ፎካክን የተመለከቱ የመነሻ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!