
ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀምን ዛሬ መገምገማቸውን ገልጸዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት በአስፈጻሚ አካላቱ በዕቅድ የተያዙ ሥራዎችና የሪፎርም አተገባበሮች ውጤታማ እንደሆኑ ተመልክተናል ብለዋል።
በቀሪ ወራት መፈፀም ያለባቸው ተግባራትን በመለየት በዓመቱ ለማሳካት የተያዙ ትልሞችን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ከሥራ ኃላፊዎች ጋር የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ነው ያሉት። በሪፖርቱ ከቀረቡ ጉዳዮች ውስጥ መልካም ውጤቶችን ማጠናከር፣ ያሉ ክፍተቶችን ማረምና በተያዘላቸው ጊዜ ያልተከወኑ ተግባራትን የማካካሻ ዕቅድ አውጥቶ በመስራት ጠንካራ አፈጻጸምን ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!