
ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ በደረሰው አሰቃቂ የሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር አብዱላሂይን በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መንግሥትና በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ለፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲና አሚር አብዱላሂይን ቤተሰቦች እንዲሁም ለኢራን ሕዝብና መንግሥትም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!