እንደ ሀገር ወደ ዲጂታላይዜሽን ለሚደረገው ሽግግር የተጀመሩ ሥራዎችን በውጤት መምራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ አሳሰቡ።

23

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ ተቋማት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በግምገማው ተጠሪ ተቋማት ሀገራዊ የልማትና የለውጥ ኢኒሼቲቮችን ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ በሚሆን መልኩ እየፈጸሙበት ያለው ሂደት በዝርዝር እንደሚገመገም ተጠቁሟል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በግምገማው የዘጠኝ ወራት ዝርዝር አፈጻጸምን በጥልቀት በመዳሰስ ለቀጣይ ተልዕኮ መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት ኢትዮጵያን ወደተሻለ ሁለንተናዊ ምዕራፍ ለማሻገር እየተተገበሩ የሚገኙ ሀገራዊ ዕቅዶችን ከማሳካት አንፃር አርዓያ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል። ለአብነትም መንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን እና መልካም አሥተዳደርን ለማሻሻል የጀመረውን የሲቪል ሰቪስ ሪፎርም ለማሳካት በቀዳሚነት እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።

እንደ ሀገር ወደ ዲጂታላይዜሽን ለሚደረገው ሽግግር የተጀመሩ ሥራዎችን በውጤት መምራት ይጠበቃል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በመድረኩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እንዲሁም የተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሀገራዊ ችግሮች ሀገር በቀል መፍትሔ!
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በዛሬው እለት ሹመቶች ሰጥተዋል።