
ሰቆጣ: ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 27ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ የ26ኛ መደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩን የ9 ወር የኦዲት ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ፣ የአሥፈጻሚውን የ9 ወር ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ እና ለተለያዩ አካላት ሹመት መስጠት በሚሉ አጀንዳዎች የሚመክር ይኾናል። የብሔረሰቡ ምክር ቤቱም ከግንቦት 12/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 13/2016 ዓ.ም ባሉ ሁለት ቀናት ድረስ የሚካሄድ ይኾናል።
ዘጋቢ፡- ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!