
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎብኝተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፣ የአሥተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን፣ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማትን ጨምሮ የተቋሙን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች አስጎብኝተዋቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን የሳይበር ደኅንነትን ለማረጋገጥ በአሥተዳደሩ እየተሠሩ ያሉ ዋና ዋና ሥራዎችን መመልከታቸው ነው የተገለጸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
