የልማት እና የሰላም ማረጋገጥ ሥራው በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ የሰሜን ሸዋ ዞን ገለጸ፡፡

21

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ግብዓትን በወቅቱ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ ሲቀጥል ሕዝቡ ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት ሰላሙን አስጠብቆ የልማት ጉዞውን እንዲያሳካ እየተደረገ እንደኾነ የሰሜን ሸዋ ዞን ገልጿል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የ2016/17 የምርት ዘመን የሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትን አጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያብራራው፡፡

በማጓጓዝ ሂደት ችግሮች እንዳያጋጥሙ የመከላከያ ሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው።

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ታደሰ ማሙሻ ሰሞኑን ወደ ይፋት ወረዳዎች የተጀመረው የማዳበሪያ ማጓጓዝ ሥራ ዛሬም ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ነው የተናገሩት።

ከ50 በላይ በኾኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ሸዋሮቢት፣ ጣርማበር እና ወደ መንዝ ወረዳዎች ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ እየተጓጓዘ ስለመኾኑም ጠቁመዋል።

የሰሜን ሽዋ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው የአርሶ አደሩን ልማት የማረጋገጥ ተግባር ከሰላም እና ፀጥታ ማስከበሩ ጎን በውጤታማነት መፈፀም መቻሉንም ነው ኀላፊው የገለጹት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተደበቀው ሃብት!
Next article“ዓላማችን ባሕር ዳር ከተማን የመማሪያ ማዕከል ማድረግ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ