“ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው” የከተማዋ ነዋሪዎች

24

ባሕር ዳር: ግንቦት 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ቃል የብሎክ እና የቀጣና ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማዕከል እና በ92 የቀጣና አደረጃጀቶች የከተማውን ማኅበረሰብ በወቅታዊ የፀጥታ፣ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ዙሪያ የምክክር እና የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የምክክር እና ውይይት መድረኩ ከግንቦት 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ነው ተብሏል። ውይይቱ ባለፉት ወራት ሕዝቡ ያነሳቸው የነበሩ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ማዕከል ያደረገ ነው። በቀጣይ መንግሥት እና ሕዝቡ በቅንጅት በሚሰሯቸው የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የሰላም ማስከበር ሥራዎችን ዙሪያ የጋራ መግባባቶቾ ተፈጥረዋል ተብሏል።

“ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው” ተወያዮቹ በቀጣይ ጊዜያትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መኾን እንዳለበት ጠቁመዋል። መረጃው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሠላም በመኾኑ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል” ተሳታፊዎች
Next article“በመጪው ክረምት አሲዳማ መሬቶችን በማከም ከፍተኛ ምርት ለማምረት እየተሠራ ነው” ግብርና ቢሮ