“ሠላም በመኾኑ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል” ተሳታፊዎች

14

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ውስጣዊ ሠላማችንን በማጽናት ውስጣዊ እና ውጫዊ ተጽዕኖዎችን በድል እንወጣለን” በሚል መሪ መልእክት በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳዳር የሕዝብ መድረክ ተካሂዷል። በሁሉም መድረኮች ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ጥልቅ ዉይይትና ምክክር ተደርጎበታል።

መንግሥት በብዙ ዉስብስብ ችግር ዉስጥ ኾኖ በርካታ ሥራዎችን በሁሉም መስክ እያስመዝገበ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ። ከሠላም አትርፈናል ሠላም በመኾኑ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልጸዋል። የሠላም መደፍረስ ያጋጠማቸው የሀገራችን አካባቢዎች ልማታቸው ተቋርጦ ለከፋ ማኅበራዊ ቀውስ መጋለጣቸውን አንስተው የዉስጥ ሰላምን በማስፈን አንድነታችንን ማጥበቅ የውጭ ጫናዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ መኾኑ ገልጸዋል።

ዘላቂ ሠላምን ለማጽናት ሁሉም ኗሪ የሰላሙ ዘብ መኾን መቻል እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ መናገራቸውን ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰላም ጥሪውን መቀበል ማሸነፍ እንጂ መሸነፍ አለመኾኑን የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next article“ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው” የከተማዋ ነዋሪዎች