
ባሕር ዳር: ግንቦት 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል እና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በመቅደላ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ክላስተርን ጎብኝተዋል፡፡ በመስክ ምልከታ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የክልሉን ሰላም ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ውጤታማ እንዲኾን በቅንጅት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
አፈ ጉባኤዋ “ሕዝቡ አንድነቱን እና ሰላሙን በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲኾኑ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል” ብለዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው በመስክ ምልከታ መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልል እና የዞን መሪዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
