“ጦርነት መፍትሔ አይደለም፤ ሰላም እንፈልጋለን” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

58

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዛሬን ቀን (ሜይ 16) “በሰላም አብሮ የመኖር ቀን” በማለት ያከብረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ወቅት ንጹሀን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚከፍሉ ይገልጻል። በጋራ በሰላም መኖር ማለት ልዩነቶችን መቀበል፣ ሌሎችን ማዳመጥ፣ ማክበር፣ እውቅና መስጠት፣ መረዳት እንዲኹም አብሮ መኖር መቻል ማለት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀኑን ዓለም አቀፍ በሰላም አብሮ የመኖር ቀን ብሎ የሚዘክረው ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ሰላምን፣ መቻቻልን፣ አካታችነትን፣ መረዳዳትን እና ትብብርን ለማጎልበት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ በማሰብ ነው። የቀኑ መዘከር ዘለቄታዊ ሰላም እና አብሮነትን ለማረጋገጥ፣ በልዩነት ውስጥ አንድነትን እና ብዝኀነትን ማዳበር የሚኖረውን ፋይዳ የማስታወስ ዓላማም አለው።

ይህ ቀን ሀገራት እርቅን በማበረታታት ሰላም እና ዘላቂ ልማት እንዲያረጋግጡም መልእክት ያስተላልፋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀኑን አስመልክቶ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ “ጦርነት መፍትሄ አይደለም፤ ሰላም እንፈልጋለን” ብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበከተሞች የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች የከተማ ገጽታ እያበላሹ እንደኾነ ተገለጸ፡፡
Next articleየአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጂንሲ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቤት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።