በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የኀብረት ሥራ ማኀበራትን ውጤታማ ለማድረግ አቅማቸውን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ።

18

ደብረ ብርሃን: ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን 921 ኀብረት ሥራ ማኀበራት እንዳሉ የኀብረት ሥራ ማኀበራት ማስፋፊያ እና ማደራጃ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ የተጠሪ ጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ባዩ ከበደ እንዚህ ማኀበራት በገንዘብ አቅማቸው እና በተቋማዊ አሠራራቸው ተወዳዳሪ ኾነው አባሎቻቸውን እና ማኀበረሰቡን በአግባቡ እንዲያገለግሉ የሚያስችል ማሻሻያ እየተደረገ ስለመኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

የፋይናንስ አገልግሎት፣ የቦታ አቅርቦት እና የፈቃድ እድሳት አገልግሎት በወቅቱ እንዲሰጣቸው ማድረግ ዋና ዋና የማሻሻያዎቹ አላማዎች ናቸው ብለዋል። ከአሁን በፊት በዘፈቀደ የሚመሩበት አሠራር ተስተካክሎ እና የደረጃ ልየታ ተደርጎ በደረጃ ውስጥ የማዋሀድ ሥራም ይከናወናል ተብሏል፡፡ ከተቀመጠው ደረጃ በታች ኾነው የተገኙ ማኀበራትን የማፍረስ ሥራ በለውጥ ማሻሻያው ተግባራዊ ይኾናል ነው ያሉት ኀላፊው፡፡

ኀብረት ሥራ ማኀበራት በተለይም የአርሶ አደሮችን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ፣ የኢንዱስትሪ ፍላጎትን ለማሳለጥ እንዲሁም ገበያን በማረጋጋት በኩል ሰፊ ሥራ ማከናወናቸውን ኀላፊው አንስተዋል፡፡

ዘጋቢ:- ወንዲፍራ ዘውዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ስምሪት በሀገር ውስጥ መሸፈን እንደማይቻል ሲረጋገጥ ብቻ መሰጠት እንደሚገባው የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleበከተሞች የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች የከተማ ገጽታ እያበላሹ እንደኾነ ተገለጸ፡፡