ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

33

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአዘርባጃን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ የተከበሩ ሚካይል ጃባሮቭ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በውይይቱም የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብሮ ለመሥራት መስማማታቸውን ተገልጿል።

የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ የተከበሩ ሚካይል ጃባሮቭ ሀገራቸው አዘርባጃን በተለይ ገቢ በማሳደግ፣ በኢንቨስትመንትና በስትራቴጂካዊ ሥራዎች ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መኾናቸውም ተጠቁሟል፡፡ የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የአዘርባጃን የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ የተከበሩ ሚካይል ጃባሮቭ ለኢትዮጵያ ልዑክ ላደረጉላቸው አቀባበል ምሥጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ”ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ውይይት አድርጓል።
Next articleየውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ስምሪት በሀገር ውስጥ መሸፈን እንደማይቻል ሲረጋገጥ ብቻ መሰጠት እንደሚገባው የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።