
ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ”ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ተጀምሯል። በመድረኩ ኢንተርፕራይዞች፣ ባለሃብቶች፣ የከተማ አሥተዳደሩ እና የክልል መሪዎች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በንቅናቄ መድረኩ አምራቾችም ምርቶቻቸውን ለሽያጭ እና ለእይታ አቅርበዋል።
ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተሠሩ ሥራዎች፣ በቀጣይም ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ይደረጋል፤ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎችም ተነስተው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
