የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የኢኖቬሽን ኤክስፖ ሊካሔድ ነው።

21

ባሕር ዳር: ግንቦት 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለ9 ቀናት የሚቆይ እና “ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ 2024” የተሰኘ ኤክስፖ ሊያካሂድ አንደኾነ ገልጿል። የፌዴራል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ.ር) እንዳሉት ሀገሪቱ የተሻለ እድገት እንድታመጣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማደግ ይገባዋል ብለዋል።

ይኽን ለማድረግ ደግሞ ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ ንቅናቄ ለመፍጠር በማስፈለጉ ኤክስፖውን ማዘጋጀት አስፈልጓል ነው ያሉት። “ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ 2024” ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፣ ምርምር፣ ዲጅታላይዜሽን እና ሥራ ፈጠራን ለማጠናከር እና ለማስተዋወቅ ዓላማ ያለው መኾኑን ዶክተር ይሽሩን ገልጸዋል።

በኤክስፖው ከ50 የግሉ ዘርፍ የአይሲቲ ኩባንያዎች፣ ከ30 የኩባንያ ፈጠራ ሥነ ምህዳር ገንቢ ተዋናዮች፣ ከ40 በላይ ባንኮች፣ የኢኮመርስ ድርጅቶች እና ከ30 በላይ የመንግሥት ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል። በሳይንስ ሙዚየም፣ በአይሲቲ ፓርክ እና በዓድዋ ሙዚየም የሚካሄደው ኤክስፖ ከግንቦት 10/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት18/2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲኾን “ሳይበር በር ይከፍታል፣ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፣ ፈጠራ ወደፊት ያራምዳል” በሚል መሪ መልዕክት ይካሄዳል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንደሚሰጥ አስታወቀ።
Next articleበግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኛ መኾኑን መንግሥት አስታወቀ።