በምዕራብ ጎጃም ዞን በምርት ዘመኑ ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ ታቅዶ እየተሠራ ነው።

16

ባሕር ዳር: ግንቦት 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2016/17 የምርት ዘመን የክረምት ሥራዎች የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው። በምዕራብ ጎጃም ዞን በ2016/17 የምርት ዘመን በ246 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያ ኀላፊው ተስፋዬ አስማረ በምርት ዘመኑ ለአርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ በማቅረብ እና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ልዩ ልዩ ሰብሎችን እና 39 ሺህ ኩንታል የቅመማ ቅመም ምርት ለማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ ዞኑ የፀጥታ ችግሮች ገጥመውት የቆዩ ቢኾንም አሁን ላይ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም እና የፀጥታ መሻሻል በመጠቀም የአርሶ አደሩ የዘር ወቅት እንዳያልፍበት የአፈር መዳበሪያ የማቅረብ ሥራ አየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

ባለሙያው የአፈር ማዳበሪያው ለሁሉም አርሶ አደር ተደራሽ እንዲኾን ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው በንቅናቄ መድረኩ ላይ የዞን እና የወረዳ የግብርና የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሰሜን ሽዋ ዞን የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ማነቆዎችን ለመፍታት እየተሠራ ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን
Next articleበሰሜን ሸዋ ዞን ያለው የባለሃብቶች ተሳትፎ የሚበረታታ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።