
ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ ምክክሮችን ለማድረግ አዘርባጃን ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት “የረጅም ጊዜ ወዳጅና አጋር ሀገር የሆነችው አዘርባጃን ገብተናል፤ ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል የሀገሪቱን መንግሥት እናመሰግናለን” ብለዋል።
በሚኖራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት መካከል በብዙ መስኮች የዘለቀውን ጠንካራ ግንኙነትና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ ምክክሮች እና ስምምነቶችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!