በዘመናዊ መንገድ የተገነባው የኮምቦልቻ ከተማ መናኸሪያ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

28

ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል መስጠት የሚያስችለው የኮምቦልቻ መናኸሪያ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። 12 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው አጠቃላይ የመናኸሪያው ግንባታ የአገልግሎት ተጠቃሚ መንገደኞች ማረፊያ፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች፣ መጸዳጃ ቤት እና ሬስቶራንቶችን ያካተተ ነው።

ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በሚሰጠው ሕንጻ ላይ 42 የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ አልጋ ቤቶች፣ 65 ሱቆች፣ አራት ደረጃቸውን የጠበቁ የካፌ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች እንዳሉት ተገልጿል።

የኮምቦልቻ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው መናኸሪያው ከ18 በላይ የመንገድ ዳር መብራቶችም ተገጥመውለታል። መናኸሪያው 114 መኪኖችን ማስተናገድ ይችላልም ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሽዋ ዞን ቡልጋ ከተማ አሥተዳድር ተገኝተው ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ።
Next articleምክር ቤቱ የገጠር መሬት አሥተዳደር እና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ፡፡