“ቅርሶች የሀገር ሃብት በመኾናቸው ተንከባክበን ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን” አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

48

አዲስ አበባ: ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የኢፌዴሪ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ፣ የኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብ፣ ስነ ጥበብ እና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማኻዲ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የባለሥልጣኑ አመራሮች ተገኝተዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ “ቅርሶች የሀገር ሃብት በመኾናቸው ተንከባክበን ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን” ብለዋል፡፡ ቅርስ ለቱሪዝም ልማት ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይኾን ማኅበራዊ ጠቀሜታም እንዲኖረው ተደርጎ እየተሠራ መኾኑን አምባሳደሯ ገልጸዋል።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ቅርሶችን የማልማቱ እንዲሁም አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች የመገንባቱ ሥራ ለቱሪዝም ዕድገቱ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ነው ያሉት። የዛሬው ጉባኤም የዚሁ አደረጃጀት ውጤት መኾኑንም አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በዘርፉ ልማት ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር እየመከረ ነው።
Next articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሽዋ ዞን ቡልጋ ከተማ አሥተዳድር ተገኝተው ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ።