የመላው ኢትዮጵያውያንን የሀገርን ምርት የመጠቀም ባሕል ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ።

31

ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመላው ኢትዮጵያውያንን የሀገርን ምርት የመጠቀም ባሕል ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሳስበዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠናቀቂያ ሥነ ሥርዓት ላይ መታደማቸውን ገልጸዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ታምርት ደግሞም ትጠቀም!” ሲሉ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዓላማው ሁለት ነው ብለዋል። የመጀመሪያው እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ዕድሎች እጅግ በተሻለ መንገድ መጠቀም ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረጉ ማነቆዎችን በቅንጅት ለመፍታት ያግዛል ሲሉ አመላክተዋል።

መንግሥት ለዘርፉ እድገት ልዩ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይኾን ያመረተችውን እንድትጠቀምም በትልቅ ትኩረት እየሠራ እንደኾነም ጠቁመዋል፡፡ “መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባሕልን እንዲያጎለብት ጥሪ እናቀርባለን” ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የባሕር ዳር ዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር
Next articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በዘርፉ ልማት ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር እየመከረ ነው።