
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ዛሬ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ መሥራች እና ፕሬዝዳንት ጄሚ ኩፐር እና ቡድናቸው ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። ድርጅቱ በሀገራችን በግብርና፣ በትምህርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ሥራዎች ሰርቷል ብለዋል።
ቢግ ዊን በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር እና ከመንግሥት ጋር በሚሠሩ በሌሎች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር አድርገናል፡፡ ይህን የትብብር ምዕራፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማምተናል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!