“ፕሮጀክቶቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ መመሪያ ሰጥቻለሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

73

ባሕር ዳር: ግንቦት 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጎንደር የሚገኙ ሦስት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የሥራ መመሪያ መስጠታቸውን አስታውቀዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በአማራ ክልል ከነበረን ቆይታ ተመልሰን ከከፍተኛ የፌደራል የሥራ ኀላፊዎች ጋር በጎንደር የሚገኙ ሦስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም ገምግመናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍጥነት የሚጠናቀቁበትን መንገድም አስቀምጠናል ብለዋል።

የፕሮጀክቶቹ ሥራዎች የመገጭ ግድብን ማጠናቀቅ፣ የጎንደር ከተማን የውኃ አቅርቦት ማሻሻል እና የአዘዞ ጎንደር 11 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራን ማጠናቀቅ ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በዛሬ ጠዋቱ ግምገማ በመመሥረት ሥራዎቹ በመጪዎቹ ወራት ተፋጥነው እንዲጠናቀቁ የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ እና “ፕሮጀክቶቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ መመሪያ ሰጥቻለሁ” ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሀገሪቱ የሙስና ፈጻሚዎች ጉዳይ አሁንም አሳሳቢ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleየብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ።