
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህም ለአንድ ጀንበር የገቢ ማሰባሰብ ላይ የተቀላቀሉ የታክሲ ማኅበር አባላትን አበረታትተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልዕክት በየመንገዱ የመጸዳዳት ጎጂ ልማድን መኮነን ብቻ ሳይኾን በመንገዶች፣ በምግብ ቤቶች፣ በሆቴሎች እና ቢሮዎች መጸዳጃ ቤቶች የመገንባትን አስፈላጊነትት ተናግረዋል።
ይህንን የጽዳት ሥራ በትብብር እንሠራለን ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ የአዲስ አበባ ታክሲ ማኅበራት ሕግ አክብሮ በመሥራት ያላቸውን ጥሩ ምግባር ለመጸዳጃ ቤት ግንባታ እና ለአካባቢ ጽዳት ለሚኖራቸው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!