ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ መሪዎች በጽዱ ኢትዮጵያ ቴሌቶን ላይ በጋራ ተሳተፉ።

55

ባሕር ዳር: ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ታላቁን የዓባይ ወንዝ ድልድይ ለማስመረቅ በባሕር ዳር ከተማ የተገኙ ከፍተኛ መሪዎች በጽዱ ኢትዮጵያ ቴሌቶን ላይ በጋራ ተሳትፈዋል። ከፍተኛ መሪዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ በውቧ የባሕር ዳር ከተማ በመገናኘት በተዘጋጀው የሒሳብ ቁጥር በአንድነት ገቢ አድርገዋል።

በጽዱ ኢትዮጵያ ቴሌቶን በአንድነት ኾነው ገቢ ካደረጉት ከፍተኛ መሪዎች ውስጥ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከፍተኛ መሪዎች ያካሄዱት ልገሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አነሳሽነት የተጀመረው ለ”ጽዱ ጎዳና፣ ኑሮ በጤና” ፕሮጀክት አንዱ ክፍል ነው ብለዋል።

ዛሬ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም እየተደረገ ባለው ንቅናቄ በአንድ ቀን ውስጥ 50 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ከፍተኛ መሪዎች የሚችሉትን ሁሉ ሲያዋጡ መቆየታቸውን ገልጸው ዛሬም በአንድነት በመኾን ለዚሁ ተብሎ ወደ ተዘጋጀው የሒሳብ ቁጥር ገቢ እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ታላቁ ድልድይ ለከተማዋ ልዩ ድምቀት እና ስጦታ ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next articleጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ ጀንበር እንቅስቃሴን ተቀላቅለዋል።