
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ የተመረቀው የዓባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው” ብለዋል።
ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው። ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል። ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!