
ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንደገለጹት ዛሬ በባሕርዳር ከተማ የተመረቀው የዓባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው። ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው ብለዋል።
ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ ነው ብለዋል። ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!