ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት የዓባይ ድልድይ ተመረቀ።

81

ባሕር ዳር: ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች ጋር በመኾን ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውን የዓባይ ድልድይ መርቀዋል።

ይኽ ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ ነው። የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የአባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ ይሆናል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአሸናፊ ግርማ ኪዳኑ ለ#ጽዱ-ኢትዮጵያ 150 ሺህ ብር ለገሱ
Next article“ኢትዮጵያ የሚገባትን፣ የአማራ ሕዝብ የሚገባውን፣ ባሕር ዳርም ለውበቷ የሚመጥን ታላቁን ሥራ በጋራ ለማስመረቅ በቅተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)