
ባሕር ዳር: ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)አሸናፊ ግርማ ኪዳኑ ለ#ጽዱ-ኢትዮጵያ 150 ሺህ ብር ለገሱ። ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ከማለዳው ሁለት ሰአት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በንቅናቄውም አሸናፊ ግርማ ኪዳኑ 150 ሺህ ብር ለግሰዋል። ከማለዳው ጀምሮ የዲጂታል ቴሌቶኑ በጠንካራ ተሳትፎ እንደቀጠለ ነው።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ እንዲቀላቀልም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!