
ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ዳዊት ይፍሩ የ ‘ጽዱኢትዮጵያ’ ዲጂታል ቴሌቶን ንቅናቄ ተቀላቅለዋል፡፡ ለ ‘ጽዱኢትዮጵያ’ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ ሁሉም ዜጋ የሚሳተፍበት የዲጂታል ቴሌቶን መካሄዱን ቀጥሏል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ይፋ የተደረገው የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይቀላቀሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!