የክፍለጦር መሪዎች እየወሰዱት ያሉት ሥልጠና ለሚመሩት አሀድ ድል አድራጊነት አጋዥ መኾኑን የምሥራቅ ዕዝ ገለጸ።

43

ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ዕዝ በብርሸለቆ ለክፍለጦር መሪዎች ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። ከሠልጣኝ መሪዎች መካከል የ74ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሸናፊ ብርቄ ሥልጠናው ስለሀገሪቱ የሠራዊት ግንባታ እና ስጋቶች ሲፈጠሩ በአነስተኛ ኀይል ስጋቶችን የምንፈታበትን መንገድ አሳይቶናል ብለዋል።

ሥልጠናው ስለወታደራዊ ስትራቴጂ፣ ዶክትሪን፣ ሰለሕዝቡ አኗኗር እንዲያውቁ እንደረዳቸው ነው ያስገነዘቡት። ሠልጥነው ሲጨርሱ ለአሀዳቸው የተማሩትን እንደሚያሥተምሩ ነው የተናገሩት። የ23ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አምሳሉ ተሰማ ፣ ሥልጠናው ከነበራቸው ልምድ እና አቅም ተጨማሪ አቅም የጨበጡበት እንደኾነ ገልጸዋል።

ዕዙ በግዳጅ መሀል አመቻችቶ እያሠለጠነ በመኾኑ ለሠራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም አመች ሁኔታ የሚፈጥር ኾኖ እንዳገኙት አብራርተዋል። የ79ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ገብረኪዳን ሀድጎ ሥልጠናው ስለ ሠራዊቱ ወታደራዊ ሥነልቦና ግንባታ ፣ ስለ ወታደራዊ ዲሲፒሊን እና ስለ ውጊያ ስትራቴጂ ያወቁበት ስለመኾኑ ተናግረዋል።

የጎጃም ኮማንድፖስት እንደገለጸው ወደ አሀዳቸው ሲመለሱ በሥልጠናው መሠረት ከበፊቱ የተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም እንደሚኖራቸው አብራርተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleውዳሴ የምርመራ ማዕከል ለጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገ።
Next articleአንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ ዳዊት ይፍሩ የ’ጽዱኢትዮጵያ’ ዲጂታል ቴሌቶን ንቅናቄ ተቀላቀሉ።