
ባሕር ዳር: ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውዳሴ የምርመራ ማዕከል ባለቤት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃይሉ ዳዊት የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽዱ ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ሳይንሳዊ እሳቤ ይዞ የመጣ እና በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጸኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል።
መንገድ ዳር መጸዳዳት ነውር ነው፣ ለጤናም ጠንቅ ነው ካልን የመጸዳጃ ሥርዓታችንን ማሻሻል ይኖርብናል። ለዚህም ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት አለባት ብለዋል። ተቋማት ነገ ይህ ዕድል አለፈኝ ብለው የማይጸጸቱበትን ዕድል ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ዳዊት በጤናው ዘርፍ ያለንን ምክረ ሃሳብ የንቅናቄው አካል በመኾን ልንገልጽ ይገባልም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!