
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የጎርጎራ ሎጅ ፕሮጀክት እና አዲሱ የዓባይ ድልድይ ፕሮጀክቶችን በማስመልከት በማኅበራዊ ገጻቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
“ውኃ እንደ ቁምነገር ሰውን ካስከበረ፤ዓባይ እና ጣና ሀገሬ ነበረ” ዓባይ በጣና ላይ ሲራመድ ታያለህ፤ ኧሯ ዓባይን በእግርህ ትወጣለህ ወይ? ይባል ነበር።
ዓባይ እና ጣና አንዱ ካንዱ ጋር አይዛመዱም፤ ጣናም የዓባይን ውኃ አያስቀርም፤ ዓባይም የጣናን ውኃ አይወስድም ይባል ነበር። የጎርጎራ ሎጅ ፕሮጀክት እና አዲሱ የዓባይ ድልድይ ዓባይ እና ጣናን አዛምደዋቸዋል። ሁለቱም ፕሮጀክቶች ጣና እና ዓባይን የሚመጥኑ ናቸው።
እናማ አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ “ውኃ እንደ ቁምነገር ሰውን ካስከበረ፤ ዓባይ እና ጣና ሀገሬ ነበረ” ማለት አሁን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!