
ባሕር ዳር: ግንቦት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሚያዝያ 18/ 2016 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ ጽዱ እና ውብ ሀገርን የመፍጠር ዓለማ አለው።
ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበር ሲኾን በፕሮጀክቱ፦
👉 የመጸዳጃ ቦታዎች ይገነባሉ።
👉 የመፋሰሻ ቦዮች ተጠርገው ይከፈታሉ።
👉 በመኖሪያ እና መሥሪያ ቤቶች አካባቢ ያሉ ቦታዎች ይጸዳሉ፣ ይለማሉ።
👉 የአመለካከት ለውጥ እንዲኖር የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ይሠራል።
👉 የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
👉 ጽዱ እና ውብ ሀገር በመፍጠር የገጽታ ግንባታ ይፈጥራል።
ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የገቢ ማሰባሰቢያ (ዲጂታል ቴሌቶን) ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቦል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!