
ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 60 ሺህ ቶን ማዳበሪያ የጫነችው ግዙፏ “ዓባይ ሁለት” መርከብ የላኘ ሴት ማዕከል በሆነው የኬንያ ላሙ ወደብ ጭነቷን ማራገፍ ጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳንን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር አላማ ያለው የላኘ ሴት ኮሪደር ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ መኾኑ ተገልጿል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር)፣ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የሎጀስቲክ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ፣ የኢትዮጵያ የባሕር እና ሎጀስቲክ አገልግሎት ዋና ሥራ አሥፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ.ር) እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች የወደቡን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ ያለውን የማዳበሪያ ጥያቄ ለመመለስ የወደብ አማራጮችን የማስፋት ሥራ እየተከናወነ መኾኑን የግብናር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የላፕ ሴት ማዕከል በኾነው የኬንያ ላሙ ወደብ ተጓጉዞ የደረሰው ማዳበሪም የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
የትራንስፓርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስትር የሎጀስቲክ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ደንጌ ቦሩ የኢትዮጵያ የገቢ እና ወጪ ምርት መጠን እያደገ በመምጣቱ የላኘ ሴት ኮሪደር ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!