በአማራ ክልል በፍትሕ ዘርፉ ያሉ መመሪያዎችን እና አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ለዜጎች ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ መኾኑ ተገለጸ።

27

ባሕር ዳር: ግንቦት 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም እንደገለጹት በፍትሕ ዘርፉ ያሉ መመሪያዎችን እና አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ለዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡

ለዚህም አዲስ የፍትሕ ተቋማት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ተነድፎ ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል። በሪፎርሙ አሳሪ መመሪያ እና ደንቦችን በማሻሻል ተደራሽ እና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ወራት ኅብረተሰቡን በማወያየት ሪፎርሙን የሚያጠናክሩ ግብዓቶች መገኘታቸውን የጠቀሱት የቢሮ ኀላፊው በሂደትም ክፍተቶችን በማስተካከል የሕግ የበላይነት እንዲከበር በመሠራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

እንዲኹም ሃሰተኛ ምስክርን የመከላከል፣ የፍትሕ ተደራሽነትን እና ጥራትን የማሳደግ ተግባራት በተሻለ ሁኔታ መከናወናቸውን ኀላፊው ተናግረዋል፡፡

የደንበኞች የአቤቱታ መዝገቦችን በፍጥነት በማየት ውሳኔ እየተሰጣቸው መኾኑን አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይም የማሻሻያ ሥራዎቹን በማስቀጠል የፍትህ ሥርዓቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ባለሃብቶች በተመረጡ የንግድ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ መፈቀዱ የሥራ እድልን ለማሥፋት ያግዛል ተባለ።
Next articleግዙፏ “ዓባይ ሁሉት” መርከብ ላሙ ወደብ ደረሰች።