
ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን የቤት ባለቤት ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በሠራዊቱ ፋውንዴሽን በኩል የቤቶች ግንባታ እና ልማት ሲከናወን ቆይቷል፡፡ ዛሬ ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋልም ተብሎ ይጠበቃል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከዚህ በፊት ተመዝግበው እና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች 1 ሺህ 236 ቤቶችን በእጣ እንደሚያስተላልፍ ነው የተገለጸው፡፡
በጋራ መኖሪያ ቤቶች የእጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የሠራዊት አባላት ተገኝተዋል።
በግልጽ አራተኛ ዙር የእጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ዛሬ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም እንደሚካሄድም ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!