
ባሕር ዳር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአሜሪካ ሰብዓዊ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በአማራ ክልል ተላላፊ በሽታዎችን እና ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚውል ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የመድኃኒት፣ ህክምና መሣሪያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ አድረጓል፡፡
በድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ድጋፉን ያሥረከቡት የአሜሪካ ሰብዓዊ ተራድኦ ድርጅት ኳሊቲ ሄልዝ ኬር አክቲቪቲ የፊልድ ኦፊሰር አሥተባባሪ ዶክተር ሠርካለም ግርማ እንደተናገሩት ድርጅቱ በክልሉ የተደረገው ድጋፍ የኮሌራ ወረርሽኝ እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ድርጅቱ በክልሉ ባሉ ዞኞች እና ወረዳዎች ድጋፍ እያደረገ መኾኑን አመስግነው የማኀብረሰቡን ጤና ለማሻሻል ሎሎች አጋር ድርጅቶችም እገዛ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!