
ባሕር ዳር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የገዳ ኢንዱስትሪ ዞን ምሥረታ ዛሬ ተካሂዷል። በምሥረታው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “በግብርና ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት በኢንደስትሪው ዘርፍ ለመድገም ትልቅ ትልም አለን” ብለዋል። የገዳ ኢንደስትሪ ዞን የሀገሪቱን እና የቀጣናውንን አቅም በመግለጥ ይህን ርዕያችንን ለማሳካት የሚረዳ ቁልፍ ተቋም ኾኖ ያገለግላል ብለዋል።
የሉሜ ነጻ የንግድ ቀጣና በኢንደስትሪ ዞን ውስጥ ኾኖ በምሥረታው ብሎም ተግባራዊ ሥራ በሚጀምርበት ወቅት ከድሬዳዋ በመቀጠል ሁለተኛው ነጻ የንግድ ቀጣና የሚሆን ሲኾን ይህም ለኢኮኖሚ እድገት እና ልማት ያሉ እድሎችን ያሰፋል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!