የሕዝባችን የዘመናት ጥያቄ እውን ኾኖ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራችን ሊፋጠን ነው።

26

ባሕር ዳር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሕዝባችን የዘመናት ጥያቄ የነበረው ታላቅ ድልድይ በታላቁ የዓባይ ወንዝ ላይ እውን ኾኖ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራችን ሊፋጠን ነው።

በውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ ተንጣሎ የሚገኘው የታላቁ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ከ60 ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ድልድዩ እድሜ ጠገብ ከመኾኑም በላይ ዘመኑን የዋጀ ፈጣን እና ተደራሽ የኾነ የሕዝብ ትራንስፖርት በመስጠት በኩል ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅን ሲፈጥር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም ምክንያት የባሕር ዳር እና አካባቢውን ሕዝብ ጨምሮ በሌሎች የውጭም ኾነ የሀገር ውስጥ ተጓዦች ላይ ሲፈጥር በነበረው ጫና የተለዋጭ ድልድይ ይገንባልን ጥያቄ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም የግንባታው ሂደት በሚገባ ተከናውኖ እነኾ ሙሉ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል ቁመና ላይ ደርሷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ109 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እያሰራጨ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።
Next articleበደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከ21 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለእርሻ መዘጋጀቱ ተገለጸ።