ከ109 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እያሰራጨ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።

16

ወልዲያ: ግንቦት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለ2016/17 የመኸር ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል 109 ሺህ ኩንታል በላይ ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ገልጿል። ለምርት ዘመኑ 159 ሺህ 197 ኩንታል ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግም የዞኑ ግብርና መመሪያ ኀላፊ ተገኝ አባተ ገልጸዋል።

በዞኑ የቅጠል ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ የደረሰ ሲሆን ከአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት ውስጥ 50 ሺህ ኩንታል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የደረሰውን ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እያከፋፈሉ እንደኾነም አብራርተዋል። የጎደለውን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ለማሟላት እየተሠራ መኾኑንም አቶ ተገኝ ተናግረዋል፡፡
አሁን ያለው የአፈር ማዳበሪያ ሚያዝያ እና ግንቦት ላይ ማሽላ ለሚዘሩ አርሶ አደሮች ቅድሚያ በመስጠት በሐምሌ ለሚዘሩት ደግሞ ቀጣይ የሚገባውን የአፈር ማዳበሪያ ለማከፋፈል መታቀዱን ተናግረዋል።

መምሪያው ከመኸር ባለፈ ለ2016 ሁለተኛ ዙር መስኖም የማዳበሪያ ግብዓት ማቅረቡን ነው የገለጹት። ከዩኒየኖች ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ሲወስዱ ያገኘናቸው የጉባላፍቶ ወረዳ አርሶ አደሮች ካለፉት ዓመት የተሻለ አቅርቦት በመኖሩ በማሳቸው ልክ ማዳበሪያ እያገኙ መኾኑን ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጡት ካንሰር አሳሳቢነት!
Next articleየሕዝባችን የዘመናት ጥያቄ እውን ኾኖ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራችን ሊፋጠን ነው።